ይፈታል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የፖለቲካ እስረኛ በእስር ቤት ህይወቱ አለፈ

pic2
pic
የመረጃው ምንጭ: ጌታቸው ሺፈራው

በእነ እስክንድር ይርጋ ክስ መዝገብ በ”በሽብር” ክስ አራት አመት ተፈርዶበት ይፈታል ተብሎ እየተጠበቀ የነበረው 2ኛ ተከሳሽ ገበየሁ ፈንታሁን በእስር ቤት ባጋጠመው የጤና እክል ህይወቱ አልፏል። ተከሳሹ በቂ ሕክምና ባለማግኘቱ ከደከመ በኋላ ወደ ፖሊስ ሆስፒታል ተወስዶ ትናንት የካቲት 18/2010 በፖሊስ ሆስፒታል ህይወቱ አልፏል።

ገበየሁ ፈንታሁን ማዕከላዊ 8 ቁጥር በሚባል ጨለማ ቤት ታስሮ እንደነበርና በቆይታው ድብደባ እንደደረሰበት በወቅቱ አብሮ ታስሮ የነበረው ጓደኛው ገልፆአል። በተለይ በአንድ ወቅት ከደረጃ ገፍትረው እንደጣሉትና በዚህም ምክንያት የራስ ህመም እንደነበረበት ተገልፆአል። አቶ ገበየሁ ፋንታሁን በታመመበት ወቅት በቂ ህክምና እንዳላገኘ ጓደኛው ገልፆአል።

pic2

አቶ ገበየሁ ፋንታሁን የአንድ ልጅ አባት እና ባለትደር እንደነበርና ከባህርዳር ተይዞ እስከታሰረበት ጊዜ ድረስ በሾፌርነት ተቀጥሮ ቤተሰቦቹን ያስተደድር እንደነበር ተገልፆአል። በክስ መዝገብ 2ኛ ተከሳሽ የነበረው አቶ ገበየሁ ፋንታሁን አራት አመት ተፈርዶበት የነበር ሲሆን 1ኛ ተከሳሽ እስከዳር ይርጋ ጥር 9/2010 ዓም ተፈትቷል። አቶ ገበየሁ ፋንታሁን ይፈታል ተብሎ እየተጠበቀ እንደነበር ታውቋል።

Be the first to comment on "ይፈታል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የፖለቲካ እስረኛ በእስር ቤት ህይወቱ አለፈ"

Leave a comment

Your email address will not be published.


*