የእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን መዝገብ የቅጣት ውሳኔ ተሰጠበት

Agibaw Setegn

የአርበኞች ግንቦት 7 አባል ናችሁ ተብለው የተከሰሱ 16 የተቃዋሚ አመራራትን የያዘው የእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን መዝገብ በባለፈው ችሎት የጥፋተኝነት ብይን መሰጠቱ የሚታወስ ነው። ሰኔ 21 ቀን በተሰጠው ብይን 3ት ተከሳሾች መከላከል ሳያስፈልጋቸው ነፃ ተብለዋል። ሰኔ 9/2009 ቀን በዋለው ችሎት 6 ተከሳሾች [1ኛ ተከሳሽ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን፣ 4ኛ ተከሳሽ አወቀ ሞኝሆዴ፣ 8ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ታሪኩ፣ 10ኛ ተከሳሽ ታፈረ ፋንታሁን፣ 13ኛ ተከሳሽ እንግዳው ዋኘው እና 15ኛ ተከሳሽ አግባው ሰጠኝ] ደግሞ ተከላከሉ ከተባሉ በኋላ፤ ክሳቸውን በበቂ በመከላከላቸው ነፃ ናችሁ ተብሎ ውሳኔ ሲሰጥ የተቀሩት 7ት ተከሳሾች ጥፋተኛ ተብለዋል።

ዛሬ ሰኔ 16 ቀን 2009 የቅጣት ውሳኔ ሲሰጥ ጥፋተኛ ከተባሉት ውስጥ 3ቱ ማለትም 3ኛ ተከሳሽ አለባቸው ማሞ መለሰ፣ 11ኛ ተከሳሽ ፈረጃ ሙሉ ዘገየ እና 16ኛ ተከሳሽ አባይ ዘውዱ ደመቀ 3ት የቅጣት ማቅለያ ተይዞላቸው ከታሰሩበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ 4 ዓመት ከ2 ወር የእስር ቅጣት ተፈርዶባቸዋል። የቀሩት 4ት ተከሳሾች ማለትም 2ኛ ተከሳሽ በላይነህ ሲሳይ፣ 9ኛ ተከሳሽ ቢሆነኝ አለነ ማረው፣ 12ኛ ተከሳሽ አትርሳው አስቻለው ተካ እና 14ኛ ተከሳሽ አንጋው ተገኘ አራጋው ሁለት የቅጣት ማቅለያ ተይዞላቸው ከታሰሩበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ 4 ዓመት ከ6ወር የእስር ቅጣት ተፈርዶባቸዋል።

አግባው ሰጠኝ በብይኑ ነፃ ተብሎ ከእስር እንዲፈታ የተፈረደ ቢሆንም ለቂሊንጦ እሳት ቃጠሎ ተጠያቂ ናችሁ ተብለው በሽብር ወንጀል ከተከሰሱት 38 እስረኞች ውስጥ አንዱ በመሆኑ በእስር ሆኖ አዲሱን ክስ የሚከታተል ይሆናል።

ባጠቃላይ በዚህ መዝገብ ስር የተካተቱት ተከሳሾች እና የተሰጣቸው ብይን
1 መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን —ከተከላከለ በኋላ ነፃ የተባለ። በአሁን ሰአት ከእስር የተፈታ
2 በላይነህ ሲሳይ ኮከቤ—4 ዓመት ከ6 ወር ፍርድ
3 አለባቸው ማሞ መለሰ—4 ዓመት ከ2 ወር ፍርድ
4 አወቀ ሞኝሆዴ ፈንታ—ከተከላከለ በኋላ ነፃ የተባለ።እስካሁን ከእስር ያልተፈታ።
5 ዘሪሁን በሬ ተረፈ—መከላከል ሳያስፈልገው ነፃ ተብሎ የተፈታ።
6 ወርቅዬ ምስጋና ዋሴ—መከላከል ሳያስፈልገው ነፃ ተብሎ የተፈታ።
7 አማረ መስፍን መለሰ—መከላከል ሳያስፈልገው ነፃ ተብሎ የተፈታ።
8 ተስፋዬ ታሪኩ በዛብህ —ከተከላከለ በኋላ ነፃ የተባለ። በአሁን ሰአት ከእስር የተፈታ።
9 ቢሆነኝ አለነ ማረው—4 ዓመት ከ6 ወር ፍርድ
10 ታፈረ ፋንታሁን አጉምሴ —ከተከላከለ በኋላ ነፃ የተባለ። በአሁን ሰአት ከእስር የተፈታ።
11 ፈረጀ ሙሉ ዘገየ—4 ዓመት ከ2 ወር ፍርድ
12 አትርሳው አስቻለው ተካ—4 ዓመት ከ6 ወር ፍርድ
13 እንግዳው ዋኘው ወርቁ—ከተከላከለ በኋላ ነፃ የተባለ። በአሁን ሰአት ከእስር የተፈታ።
14 አንጋው ተገኘ አራጋው—4 ዓመት ከ6 ወር ፍርድ
15 አግባው ሰጠኝ በሪሁን —ከተከላከለ በኋላ ነፃ የተባለ። በእስር ሆኖ ሌላ ክስ የሚከታተል።
16 አባይ ዘውዴ ደመቀ—4 ዓመት ከ2 ወር ፍርድ


Photo: አግባው ሰጠኝ በሪሁን

Please click here to see summary of the charges in English

Be the first to comment on "የእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን መዝገብ የቅጣት ውሳኔ ተሰጠበት"

Leave a comment

Your email address will not be published.


*