ከአይ ኤስ አይ ኤስ (ISIS) ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው 26 ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

ISIS

ከአይ ኤስ አይ ኤስ ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው 26 ተከሳሾች (እነ በክሪ አወል) በ24/4/2010 የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡፡

የተከሳሾች ስም ዝርዝር:

1ኛ በክሪ አወል ሃሰን

2ኛ መሀመድ ሃሰን አደም

3ኛ ጀማል ጥበቡ በሱፍቃድ

4ኛ አሊ ሽፈራው ሰኢድ

5ኛ አብዱ ሙስጠፋ መሀመድ

6ኛ ኢብራሂም አብዱ መሀመድ

7ኛ ጅብሪል ሃሰን ሰይድ

8ኛ አሊ ጀማል አብዲ

9ኛ አህመድ መሀመድ ኬቦ

10ኛ መሀመድ አህመድ መሀመድ

11ኛ ጀማል መሀመድ አወል

12ኛ ጀማል ኑር ሀሰን ካህሳይ

13ኛ ሰይድ ኢብራሂም አህመድ

14ኛ ሙራድ ተማም መሀመድ

15ኛ ኑር ዘመን ሰሌማን አባቡልጉ

16ኛ መሀመድ መኪይ ሀሰን አደም

17ኛ ሳዳም ሁሴ ጁዋር

18ኛ ወንድወሰን ወልዴ ሀ/ማርያም

19ኛ ራህማቶ አድነው አሰፋ

20ኛ ኑረዲን መሀመድ አወል

21ኛ ሐረሙ ሲራጅ አስፋው

22ኛ አሊ ኢብራሂም ይማም

23ኛ አብዲ መሀመድ ሙሳ

24ኛ አብዱ አህመድ አደም

25ኛ ሉሉ አክሊሉ ጌጡ

26ኛ አህመድ መሀመድ አወል

የክሱ ዝርዝር

1ኛ ክስ፡- ከ1ኛ እስከ 3ኛ እና 26ኛ ተከሳሾች ላይ የቀረበ ክስ ነው፡፡ክሱ ከአይ ኤስ ኤስ ቡድን ጋር ግንኙነት ፈጥረው ስልጠና በመውሰድ እና በኢትዮጵያ በመመለስ የጅሃድ ጦርነት ለማወጅ በማሰብ በአዲስ አበባ፣ ሃረር እና አላባ ውስጥ የሚገኘውን የቡድኑን አደረጃጀት በበላይነት በመፍጠር በ2001 የወጣውን የፀረሽብርተኝነት አዋጅ አንቀፅ 7(2) ን በመተላለፋቸው እንደሆነ ይገልፃል፡፡

2ኛ ክስ፡- ከ4ኛ እስከ 25ኛ ተከሳሾች ላይ የቀረበ ክስ ነው፡፡ ክሱ ከአይ ኤስ ኤስ ቡድን ጋር ትስስር በመፍጠር እና 1ኛ ክስ በቀረበባቸው ግለሰቦች አስተባባሪነት የሽብር ቡድኑን ስልጠናዎች የሚወስዱበትን ሁኔታ በማመቻቸት በመንቀሳቀሳቸው በ2001 የወጣውን የፀረሽብርተኝነት አዋጅ አንቀፅ 7(1) ን በመተላለፋቸው እንደሆነ ይገልፃል፡፡

በ24/4/2010 ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ችሎት የቀረቡት የክስ መቃወሚያ ካላቸው ለመቀበል ነበር፡፡ ሆኖም ተከሳሾቹ የክስ መቃወሚያ የለንም በማለታቸው የእምነት ክህደት ቃል እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡ 10ኛ፣ 17ኛ እና 23ኛ ተከሳሾች “ጥፋተኛ ነን፡ ወንጀሉን ፈፅመናል” ሲሉ የተቀሩት “ወንጀል አልፈፀምንም ጥፋተኛም አይደለንም” ሲሉ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ አቃቤ ህግም ምስክሮቹን አቅርቦ እንዲያሰማ እንዲሁም ጠፋተኛ ነን ያሉ ተከሳሾችም የሰጡት የእምነት ቃል ታይቶ ብይን እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡ ጥፋተኛ አይደለንም ያሉ ተከሳሾች ላይ የሚቀርቡ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ግንቦት 9፣ 13፣ 14፣ 15፣ 16 እና 21 ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ ጥፋተኛ ነን ላሉ ተከሳሾች ደግሞ ለብይን ጥር 7 ቀን እንዲቀርቡ ተብለዋል፡፡ ተከሳሾቹ ማእከላዊ ከ6 ወር በላይ መቆየታቸውን እንዲሁም 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ሙስሊም በመሆናቸው እና በእምነት አልባሳቸው ምክንያት ዞን 5 የሚባል ቦታ ከሌሎች እስረኞች ተገልለው የአእምሮ በሽተኛ የሆኑ እስረኞች ተለይተው የሚቀመጡበት ክፍል እንዳስገቧቸው ተናግረዋል፡፡ የዋልድባ ገዳም መነኩሴ የሆኑት አባ ገ/ስላሴም ከእነሱ ጋር ተገለው እንዲቀመጡ ገልፀዋል፡፡ አቤቱታቸውን ያቀረቡት ተከሳሾች ጥያቄያቸውን በፅሁፍ አድርገው እንድታቀርቡ ተብለዋል፡፡

 ሙሉ ክሱን ለማየት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።

Be the first to comment on "ከአይ ኤስ አይ ኤስ (ISIS) ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው 26 ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ"

Leave a comment

Your email address will not be published.


*