አዲስ: ፀሃፊ አመንቲ ሎኮ እና ሌሎች 2 ወጣቶች የክሳቸው ይዘት ተነቦላቸዋል

Amenti

ቀን  4/4/2010

Onnee Dhugaan Madeesse እንዲሁም Imimmaan Ummataa የተሰኙት መጽሃፍትን የጻፈው አመንቲ ሎኮ ጉተማ ዛሬ ከቂሊንጦ እስር ቤት ልደታ ወደሚገኘው ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ቤት ቀርበው የክሳቸው ይዘት ተነቦላቸዋል።

አመንቲ ሎኮ Imimmaan Ummataa የሚለውን አዲሱን መጽሃፉን ካሳተመ ከአንድ ወር በኋላ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች እየተዘዋወረ በመሸጥ ላይ ሳለ ቡሌ ሆራ ላይ የየፌደራል ጸጥታ ሃይሎች አፍነውት ማዕከላዊ አስገቡት። ማዕከላዊ ውስጥ ብዙ ድብደባና ቶርቸር ካፈጸሙበት በኋላ ወደ ቂሊንጦ ወስደውት ዛሬ ደሞ ልደታ በሚገኘው የፌደራል ፍርድ ቤት  የሽብር ክስ ይዘት ተነቦላቸዋል።

አቃቤ ህጉም ምስክር አለኝ ብሏል። እናም ለ12/4/2010 ቀጠሮ ተሰጥቷል። ከአመንቲ ሎኮ ጋር የቀረቡት ሁለተኛ ተከሳሽ ድርባ ተመስገን (እድሜ 26 ፤ የሻሸመኔ ነዋሪ) እንዲሁም ሶስተኛ ተከሳሽ አብዱራህማን ኤደኦ (እድሜ 26 ፤ የአርሲ ነገሌ ነዋሪ) ናቸው።

ተከሳሾቹ ሁሉም አማርኛ ቋንቋ መናገር አይችሉም።

 ሙሉ ክሱን ለማየት ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።

Be the first to comment on "አዲስ: ፀሃፊ አመንቲ ሎኮ እና ሌሎች 2 ወጣቶች የክሳቸው ይዘት ተነቦላቸዋል"

Leave a comment

Your email address will not be published.


*