አዲስ: የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በእነ ዮሐንስ መንግስቴ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላለፈ

Yohanes

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት ኤርትራ በመሄድ የሽብር ቡድን ወታደራዊ ስልጠና በመውሰድ ኢትዮጵያ ገብተው የሽብር ተግባር ውስጥ ተሰማርተው ተገኝተዋል የተባሉ 6 ግለሰቦች ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላለፈ፡፡

ተከሳሾቹ ዮሐንስ መንግስቴ፣ ፀጋዬ ዘለቀ፣ ጋሻው ሙልዬ፣ ማንአስቦህ ብርሃኑ፣ አስማረ ግለጥ አድማሱ እና ጉርባ ወርቁ የተሰኙ ናቸው፡፡

እንደ ፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ተከሳሾቹ ራሱን የአርበኞች ግንቦት ሰባት ብሎ ከሚጠራው የሽብር ቡድን ከየካቲት 2ዐዐ2 እስከ የካቲት እስከ 2ዐዐ8 በተለያዩ ጊዜያት ለ3 ወራት ያህል ኤርትራ ውስጥ ሃረና ተብሎ በሚጠራው ማሰልጠኛ የሽብር ቡድኑ ታጣቂ በመሆን ተንቀሣቅሰዋል፡፡

ከስልጠናቸው በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ የሽብር ቡድን መመልመል፣ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ቤዝ መምረጥ፣ የሽብር ቡድኑን ለማጠናከር ገንዘብ መዝረፍ፣ የመንግስት ተቋማትን ማውደምና የፀጥታ ሃይል ላይ ጥቃት መፈፀም የወንጀለኞቹ አላማ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

ይህንን አላማ ይዘው ወደ ኢተዮጵያ ገብተው በሰሜን ጐንደር ዞን አርማጭሆ ወረዳ ዘመነ በርቅ እና መተማ ላስታ ቀበሌ ተኩስ በመክፈት አንድ ሰው በመግደል ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት በማድረስ ታህሳስ 2ዐዐ8 በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ተከሳሾቹ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በእነዚህና ተያያዥ የሽብር ወንጀሎች ያቀረበባቸውን የወንጀል ክሶች ክደው በመከራከራቸው የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ አስመስክሮባቸዋል፡፡

ችሎቱ በፀረ-ሽብር አዋጁ አንቀፅ 3 እንዲከላከሉ ብይን ቢሰጥም መከላከል እንደማይፈልጉ መግለፃቸውን ተከትሎ፣ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት ሁሉም ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል፡፡

የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለታህሣስ 24 ቀን 2ዐ1ዐዓ ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

ምንጭ: EBC

 

Be the first to comment on "አዲስ: የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በእነ ዮሐንስ መንግስቴ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላለፈ"

Leave a comment

Your email address will not be published.


*