አዲስ: የዋልድባ መነኮሳት ምስክር ሊሰማባቸው ነው

waldba
የመረጃው ምንጭ: ጌታቸው ሺፈራው

በእነ ተሻገር ወ/ሚካኤል ክስ መዝገብ የ”ሽብር” ክስ የተመሰረተባቸው የዋልድባ መነኮሳት ለመጋቢት 18/2010 ዓም ምስክር ይሰማባቸዋል ተብሏል።

በእነ ተሻገር ወ/ሚካኤል ክስ መዝገብ ተከሰው ከነበሩት 35 ተከሳሾች መካከል 32ቱ ክሳቸው ተቋርጦ የተፈቱ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ ነጋ ዘላለም መንግስቴ፣ 4ኛ ተከሳሽ አባ ገ/ እየሱስ ኪ/ማርያም እና 5ኛ ተከሳሽ አባ ገ/ስላሴ ወ/ሐይማኖት ብቻ ክሳቸው ቀጥሏል።

የዛሬው የካቲት 19/2010 ዓም ቀጠሮ ተይዞ የነበረው በመዝገቡ ከተጠቆጠሩት ምስክሮች መካከል ጉዳያቸው ይቀጥላል በተባሉት 3ቱ ተከሳሾች ላይ የሚቀርቡትን አቃቤ ህግ ለይቶ እንዲያስመዘግብ እና መነኮሳቱ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ነበር። በዚህም መሰረት 1ኛ፣ 2ኛ እና 4ኛ ምስክሮች በመነኮሳቱ እና በ2ኛ ተከሳሽ አቶ ነጋ ዘላለም ላይ ይመሰክራሉ ተብሏል። የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማትም ለመጋቢት 18 ቀጠሮ ተይዟል።

በሌላ በኩል የቂሊንጦ እስር ቤት መነኮሳቱ የምንኩስና ልብሳቸውን እንዲያወልቁ እንያገደዳቸው መሆኑን ለፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን እስር ቤቱ ለካቲት 30 መልስ እንዲሰጥ ታዟል።

4ኛ ተከሳሽ አባ ገ/እየሱስ ኪ/ማርያም እና 5ኛ ተከሳሽ አባ ገ/ስላሴ ወ/ሐይማኖት ልብሳቸውን አናወልቅም በማለታቸው ባለፉት ቀጠሮዎች ያልቀረቡ ሲሆን በአቤቱታቸው ላይ ቅጣት ቤት እንደሚገኙ መግለፃቸው ይታወሳል። የሁለቱም መነኮሳት አካል ላይ ባለፉት ጊዜያት ያልነበረ ጉስቁልና ይስተዋላል።

የክስ ዝርዝር ብዛት:  34 ገፅ

Be the first to comment on "አዲስ: የዋልድባ መነኮሳት ምስክር ሊሰማባቸው ነው"

Leave a comment

Your email address will not be published.


*