አዲስ: የእነ ተሾመ ረጋሳ መዝገብ ብይን ትላንትና ተነበበ

Teshome

ሰባቱ ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ የሚያስረዳ ማስረጃ ባለመገኘቱ በነፃ እንዲሰናበቱ፤ የተቀሩት 9ኙ ደግሞ እንዲከላከሉ የሚል ብይን ተሰጥቷል

 

በምእራብ ሸዋ ዞን በአንቦ እና አጎራባች ከተሞች ማስተር ፕላኑን እንደ ሽፋን በመጠቀም ከ2006 ጀምሮ የሽብር ተግባር ለመፈፀም ሲያሴሩ፣ ሲያቅዱ እና ሲፈፅሙ ነበሩ ተብለው የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው የእነ ተሾመ ረጋሳ መዝገብ ትላንትና ብይን ተነበበ።

በ2008 መጀመሪያ ላይ ታስረው ሃምሌ ወር 2008 ላይ ክስ የተመሰረተባቸው እነ ተሾመ ረጋሳ ሁለት ክስ ቀርቦባቸው ነበር።

1ኛ ክስ በ2ኛ፣ በ3ኛ እና ከ5–15ኛ ባሉ ተከሳሾች ላይ የፀረሽብር ህጉን አንቀፅ 4 በመተላለፍ የቀረበ ክስ፤ 2ኛ ክስ በ1ኛ፣ 4ኛ እና 16ኛ ተከሳሾች ላይ የፀረ ሽብር ህጉን አንቀፅ 3 (1) እና (4) ን በመተላለፍ የቀረበ ክስ ነው።

አቃቤ ህግ ያቀረባቸው የሰው፣ የሰነድ እና የሲዲ ማስረጃዎች ተመርምረው ዛሬ ብይኑ ተነቦላቸዋል። በተነበበው ብይን ሰባቱ ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ የሚያስረዳ ማስረጃ ባለመገኘቱ በነፃ እንዲሰናበቱ፤ የተቀሩት 9ኙ ደግሞ እንዲከላከሉ የሚል ብይን ተሰጥቷል። 1ኛ ተከሳሽ ተሾመ ረጋሳ የተከሰሰበትን አንቀፅ [የፀረሽብር ህጉን አንቀፅ 3 (1) እና (4) ] እንዲከላከል 2ኛ ተከሳሽ ጫላ ዲያስ በፀረሽብር ህጉ አንቀፅ 4 መሰረት የቀረበበትን ክስ እንዲከላከል 3ኛ ተከሳሽ ኦብሱማን ኡማ በፀረሽብር ህጉ አንቀፅ 4 መሰረት የቀረበበትን ክስ እንዲከላከል 4ኛ ተከሳሽ ኒሞና ለሜሳ የተከሰሰበት አንቀፅ (የፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ 3) ተቀይሮ በፀረሽብር ህጉን አንቀፅ 4 መሰረት እንዲከላከል 5ኛ ተከሳሽ ከበደ ጨመዳ የቀረበበትን ክስ መከላከል ሳያስፈልገው በነፃ እንዲሰናበት 6ኛ ተከሳሽ ምህረቱ ጉልማ የቀረበበትን ክስ መከላከል ሳያስፈልገው በነፃ እንዲሰናበት 7ኛ ተከሳሽ ዴቢሳ በየነ የቀረበበትን ክስ መከላከል ሳያስፈልገው በነፃ እንዲሰናበት 8ኛ ተከሳሽ ጌታሁን ደስታ በፀረሽብር ህጉ አንቀፅ 4 መሰረት የቀረበበትን ክስ እንዲከላከል 9ኛ ተከሳሽ መንግስቱ ጉዲሳ የቀረበበትን ክስ መከላከል ሳያስፈልገው በነፃ እንዲሰናበት 10ኛ ተከሳሽ ተሰማ ሁንዴ በፀረሽብር ህጉ አንቀፅ 4 መሰረት የቀረበበትን ክስ እንዲከላከል 11ኛ ተከሳሽ ቦንሳ ሃይሉ የቀረበበትን ክስ መከላከል ሳያስፈልገው በነፃ እንዲሰናበት 12ኛ ተከሳሽ አሸብር ኮንሾ በፀረሽብር ህጉ አንቀፅ 4 መሰረት የቀረበበትን ክስ እንዲከላከል 13ኛ ተከሳሽ ጃራ ኤቢሳ የቀረበበትን ክስ መከላከል ሳያስፈልገው በነፃ እንዲሰናበት 14ኛ ተከሳሽ ፉፋ ሬፋንራፋ በፀረሽብር ህጉ አንቀፅ 4 መሰረት የቀረበበትን ክስ እንዲከላከል 15ኛ ተከሳሽ አጥናፉ ዲሳሳ የቀረበበትን ክስ መከላከል ሳያስፈልገው በነፃ እንዲሰናበት 16ኛ ተከሳሽ አብዲ ታደሰ የተከሰሰበትን አንቀፅ [የፀረሽብር ህጉን አንቀፅ 3 (1) እና (4) ] እንዲከላከል።

በነፃ እንዲሰናበቱ የተባሉት ተከሳሾች በሌላ ክስ የማይፈለጉ ከሆነ ማረሚያቤት እንዲፈታቸው፤ እንዲከላከሉ የተባሉት ተከሳሾች ደግሞ ጥር 24 ቀን መከላከያ ማስረጃዎቻቸውን ማሰማት እንዲጀምሩ ትእዛዝ ተሰጥቷል።

Be the first to comment on "አዲስ: የእነ ተሾመ ረጋሳ መዝገብ ብይን ትላንትና ተነበበ"

Leave a comment

Your email address will not be published.


*