አዲስ: የእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ጉዳይ:: በሁለት ሳምንታት ውስጥ የተካሄደውን የአቃቤ ህግ የምስክር ማሰማት ሂደት በ25 ገፅ ዘርዝረን አቅርበነዋል

Qilinto 38

 

 

የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ለመከሰቱ ፣ ለጠፋው የሰው ህይወት እና ንብረት ተጠያቂ ናችሁ ተብለው የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው 38 እስረኞች (እነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ) ባለፉት ሁለት ሳምንቶች አቃቤ ህግ በተያዘለት ቀጠሮ መሰረት ምስክሮቹን አቅርቦ ሲያሰማ ነበር።

አቃቤ ህግ ምስክር እንዲያሰማ ከተሰጠው 9 ቀን ውስጥ በ 4ቱ ቀን ብቻ አምስት ምስክሮችን አቅርቦ ያሰማ ሲሆን በተቀሩት አምስት ቀናት ምስክሮቹን ማቅረብ ሳይችል ቀርቷል።

አቃቤ ህግ ቀሪ 28 ምስክሮቹን እንዲያሰማ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠው ቢጠይቅም፤ “አቃቤ ህግ የተሰጠውን በቂ ጊዜ በአግባቡ አልተጠቀመም” እንዲሁም “የተከሳሾችን የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብት የሚጋፋ ነው” በማለት ዳኞቹ አቃቤ ህግ ሁለት መጥሪያ ደርሷቸው ከቀሩ ምስክሮቹ ውጪ ያሉትን ምስክሮቹ የማሰማት መብቱ እንዲታለፍ ወስነዋል።

ፈርመው የቀሩ ሁለት የአቃቤ ህግ ምስክሮች ታስረው እንዲቀርቡ እና ለጥር 18/2010 እንዲሰሙ ቀጠሮ ተይዟል።

 በባለፉት ሁለት ሳምንታት በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ መዝገብ የነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ለማግኘት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።

 

የእነ ማስረሻ ሰጤ ሙሉ ክሱን ለማየት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።

የእነ ማስረሻ ሰጤ በእንግሊዘኛ የተተረጎመ የክስ ዝርዝር እንዲሁም የተከሳሾችን ተጨማሪ ፎቶዎች ለማግኘት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።

Be the first to comment on "አዲስ: የእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ጉዳይ:: በሁለት ሳምንታት ውስጥ የተካሄደውን የአቃቤ ህግ የምስክር ማሰማት ሂደት በ25 ገፅ ዘርዝረን አቅርበነዋል"

Leave a comment

Your email address will not be published.


*