አዲስ: የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባል ሆናችሁ ስትንቀሳቀሱ ነበር ተብለው ከተከሰሱት የአርባምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ፍርድ ትላንት በ4ኛ ችሎት ተነበበ

pg7

የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባል ሆናችሁ ስትንቀሳቀሱ ነበር ተብለው ከተከሰሱት የአርባምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ፍርድ ትላንት በ4ኛ ችሎት ተነበበ።

በአርባምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሆነውን አቶ ሉሉ መሰለን ጨምሮ ሌሎች 12 ሰዎች ባጠቃላይ 13 ሰዎች የፀረ ሽብር ህጉን አንቀፅ 7(1) ተላልፋችኋል ተብለው ጥቅምት ወር 2008 የታሰሩ ሲሆን፤ በብይን አንድ ተከሳሽ ነፃ ሲወጣ የጠቀሩት 12ቱ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶ ነበር። ተከላከሉ ከተባሉት ውስጥ አምስቱ መከላከያ ማስረጃ ማቅረብ እንደማይፈልጉ በመግለፃቸው መጋቢት ወር 2009 ላይ 4ዓመት ከ5ወር የእስር ቅጣት ተበይኖባቸዋል።

የተቀሩት 7ቱ መከላከያ ማስረጃዎቻቸውን የሲያሰሙ ቆይተው ከ2009 መጨረሻ ጀምሮ ለፍርድ ሲቀጠሩ ነበር። በርካታ ተለዋጭ ቀጠሮዎች ከተሰጡ በኋላም ዛሬ ብይኑ ተነቦላቸዋል። ሁሉም የተከላከሉት ተከሳሾች [ሉሉ መለሰ፣ አየለች አበበ፣ በጋሻው ዱንጋ፣ ዘኪዎስ ዘሪሁን፣ ጌታሁን ቃፃ፣ መርደኪዎስ ሽብሩ እና ያረጋል ሙሉአለም] እንዲከላከሉ የተባለውን ክስ በአግባቡ ባለመከላከላቸው በዛው በተከሰሱበት አንቀፅ ጥፋተኛ መባላቸውን ተነቦላቸዋል።

ጥር 8 ቀን 2010 ለቅጣት ውሳኔ የተቀጠሩ ሲሆን ከዛ በፊት የቅጣት ማቅለያ ካላቸው በሬጅስትራር በኩል እንዲያስገቡ ተነግሯቸዋል።

Be the first to comment on "አዲስ: የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባል ሆናችሁ ስትንቀሳቀሱ ነበር ተብለው ከተከሰሱት የአርባምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ፍርድ ትላንት በ4ኛ ችሎት ተነበበ"

Leave a comment

Your email address will not be published.


*