አዲስ: የቂሊንጦ እስር ቤት መነኮሳቱን ልብሳቸውን እንዲያወልቁ አስገደዳቸው

monks1

monks1

የዜናው ምንጭ ጌታቸው ሽፈራው

የቂሊንጦ እስር ቤት መነኮሳቱን ልብሳቸውን እንዲያወልቁ አስገደዳቸው። “አናወልቅም” ሲሉ መሬት ላይ ተጎተቱ። ይህን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4 ወንጀል ችሎት አመልክተው ለዛሬ ቀጠሮ ተሰጥቶ ነበር።

ፍርድ ቤቱ ይህን የሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ ብይን መስጠት አልቻለም። “አልሰራነውም” ብሏል።

ጠበቃ አምሃ መኮንን አባ ገ/እየሱስ ኪዳነ ማርያም ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ በመግለፅ በአስቸኳይ ብይን ሊሰጥ እንደሚገባ ለፍርድ ቤት አመልክተዋል። ፍርድ ቤቱ ግን ይህን አቤቱታም አልሰራነውም በሚል ለመጋቢት 10 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

“የእምነት ልብስ ይፈቀድ? አይፈቀድ?” ብቻ አይደለም። ጨለማ ቤት ያለ ሰውን ጉዳይ ለመበየን ነው ይህ ሁሉ ቀጠሮ!

በአንድ ወቅት ፀበሉን “ውሃ ነው” ተብለዋል። ልብሳቸውን አውልቁ እየተበሉ ነው። ውርደቱ ለሁለቱ አባቶች የሚመስለው ካለ በጣም ይገርማል። የእስር ቤቱ ነውር፣ የፍትህ እጦቱ እምነት ላይ የተቃጣ ነው! ግን ቄሶችም ዝም ብለዋል! አማኞች ዝም ብለዋል!

Be the first to comment on "አዲስ: የቂሊንጦ እስር ቤት መነኮሳቱን ልብሳቸውን እንዲያወልቁ አስገደዳቸው"

Leave a comment

Your email address will not be published.


*