አዲስ: እነ ደቻሳ ዊርቱ ሞሲሳ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ

Chaltu TakeleShe was a 2nd year sociology student at Addis Ababa University (3)

 

1ኛ ተከሳሽ ደቻሳ ዊርቱ ሞሲሳ፣ 2ኛ ተከሳሽ አለሙ ተሾመ፣ 3ኛ ተከሳሽ ጫልቱ ታከለ።

ውጪ ካሉ የኦነግ አባላት ጋር በመነጋገር፣ ገንዘብ በመቀበል የውትድርና ስልጠና ኤርትራ ሄደው ለመሰልጠን ወስነው በመንገድ ላይ እያሉ ተይዘዋል ተብለው የፀረሽብርተኝነት ህጉ አንቀፅ 7(1) ተጠቅሶባቸው ነው ክስ የቀረበባቸው።

ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ቢሮ ስልክ በመጥለፍ ተገኘ የተባለ የፅሁፍ ሪፖርት እና በማእከላዊ እያሉ ተከሳሾቹ ለፖሊስ የሰጡት ቃል ብቻ ነው በማስረጃነት የቀረበባቸው። የቀረበባቸው የሰነድ ማስረጃዎች አቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ በበቂ ያስረዳል በማለት ዳኞች እንዲከላከሉ በማለት ዛሬ (ህዳር 28/2010) ብይን ሰጥተዋል።

3ኛ ተከሳሽ የሆነችው ጫልቱ ” ከደህንነት ቀረበ የተባለው ሪፖርት ኤርትራ ስለመሄዳችን የሚያወራው ነገር በሌለበት ሁኔታ ተከላከሉ ብላችሁ ብይን መስጠታችሁ አሳዝኖናል። ከኢህአዴግ ፍርድ ቤት ምንም አንጠብቅም። ወደፊትም ፍትህ እንደማናገኝ ነው የምናስበው። ” ስትል የመሃል ዳኛው “ለፖሊስ ቃል አልሰጠሽም?” ብለው ሲጠይቋት “ለፖሊስ የሰጠሁትም ቃል ሱዳን ለስራ እየሄድኩ እንደሆነ ነው የሚያወራው። ሱዳን መሄድ እና መስራት ደግሞ መብቴ ነው። ” ስትል መልሳላቸዋለች። ዳኛውም “እሱን ክስሽን ስትከላከይ ታቀርቢዋለሽ ብለዋታል።”

በመጀመሪያ ስትታስር ጫልቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ አመት የሶሲዮሎጂ ተማሪ ነበረች።

ቀሪዎቹ ሁለቱ ተከሳሾችም አስተያየት እንዳላቸው እና እንዲናገሩ ቢጠይቁም ሳይፈቀድላቸው ቀርቷል። ጫልቱ በተናገረችው ንግግር እላፊ ተናግረሻል ተብላ ችሎት በመድፈር ጥፋተኛ ብለዋታል። ማስረጃዎቹ በአግባቡ ሳይመዘኑ ተከላከሉ የሚል ብይን በመሰጠቱ አዝና በመበሳጨቷ በስሜት ሆና መናገሯን የገለፀች ሲሆን ቅጣቱ በብር ወይም በእስር እንዲሆንላት ተጠይቃ በብር እንዲደረግላት መርጣለች።

የቅጣቱ ውሳኔ በአዳሪ ለነገ ቀርባ እንድትሰማ ተቀጥራለች። ተከሳሾቹ መከላከያ ምስክሮቻቸውን እና ማስረጃቸውን እንዲያቀርቡ ለየካቲት 12/2010 ተቀጥረዋል።

***ሙሉ ክሱን (3ገፅ) ለማግኘት   ይህንን ሊንክ ይጫኑ።

Be the first to comment on "አዲስ: እነ ደቻሳ ዊርቱ ሞሲሳ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ"

Leave a comment

Your email address will not be published.


*