ተከሳሽ: አቶ እዩእል ሙራቴ ወንጅን

Ato Eyuel

 

ቀን 09/03/2008

የፌ/ማ/ዐ/ሕ/መ/ቁ 179/08

በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት

አዲስ አበባ

ከሳሽ    የፌ/ማ/ዐ/ ሕግ

ተከሳሽ አቶ እዩእል ሙራቴ ወንጅን

ስራ : ገበሬ

አድራሻ : ጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን ጉደሬ ወረዳ ዱንቻዬ ከተማ

አንደኛ ክስ

በኢፌድሪ ወ/መ/ ህግ 144/1996 አንቀፅ 32/1/ሀ/ለ እና አንቀፅ 240/3  የተደነገገውን በመተላለፍ በዋና ወንጀል በቀጥታ እና በዕጅ አዙር በመሳተፍ፣ በጦር መሳርያ የተደገፈ ዐመፅ በማንሳት የትጥቅ ትግል በማነሳሳት

  • በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል ሸካ ዞን የኪ ወረዳ ፃኑ እና ዳርሙ ቀበሌዎች፣ በጉፍታ ንዑስ ቀበሌ ከግብረ አበሮቹ በእነ አማኑኤል የማሎ በመ/ቁ 164221 ከተከሰሱ ጋር በመሆን በፖሊስ እና በህዝብ ላይ ጉዳት በማድረስ.፣ በጋምቤላ ክልል ማዣንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ ዱንቻይ ቀበሌ ከሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30/2007 ድረስ በጦር መሳርያ የተደገፈ ዐመፅ በማንሳት የትጥቅ ትግል በመጀመርና በማደራጀት ክላሺንኮቭ በመያዝ የእርስ በእርስ ግጭት በማነሳሳት እንዲሁም ንብረት በማውደምና በመንግስት እና በህዝብ ላይ ጉዳት እንዲደርስ በማድረግ፤ ከሰኔ2 እስከ ሰኔ 26/2007 የግል ተበዳዮች የአቶ ዋሲሁን ገበየሁን፣የአቶ ኤልያስ ኩሽንን እና የአቶ ጋይዳ መኮንንን  ቤት ቃጠሎ ላይ በቀጥታ በመሳተፍ፤ በጥቅምት 15/2007 የፌዴራል ፖሊስ ካምፕ በጦር መሳርያ በማጥቃት

ሁለተኛ ክስ

በኢፌድሪ ወ/መ/ ህግ አንቀፅ 240/4 የተደነገገውን በመተላለፍ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ፣ አንቀፅ 32/1/ሀ/ የተደነገገውን በመተላለፍ፣ አንቀፅ 539/1/ሀ የተደነገገውን በመተላለፍ አስቀድሞ በታቀደ ከባድ የሰው ግድያ በመፈፀም

  • በሰኔ 26/2006 ዓ.ም የግል ተበዳይ አቶ መንገሻ ወርቁን በአሰቃቂ ሁኒታ ቆራርጦ በመግደል፤

ሦስተኛ ክስ

በኢፌድሪ ወ/መ/ ህግ አንቀፅ 240/4፣ አንቀፅ 32/1/ሀ እንዲሁም በአንቀፅ494/2 የተደነገገውን በመተላለፍ የእሳት ቃጠሎ በማድረስ

  • በሰኔ 26/2006 ዓ.ም አቶ ዋሲሁን ገበየሁን በጦር መሳርያ አስፈራርቶ አባሮ ቤት በማቃጠል

አራተኛ ክስ

በኢፌድሪ ወ/መ/ ህግ አንቀፅ 240/4፣ አንቀፅ 32/1/ሀ እንዲሁም በአንቀፅ494/2 ተከሰዋል፡፡

  • በሰኔ 26/2006 የአቶ ጋይዳ መኮንንን ቤት በማቃጠል

የማስረጃ ዝርዝር

  • የሰነድ ማስረጃ 1/ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል ለሸካ ዞን አስ ፅ/ቤት የተፃፈ

2/ የሟች አቶ መንገሻ ወርቁ የህክምና ማስረጃ

3/ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል በሸካ ዞን የኪ ወረዳ አስ ፅ/ቤት ለፌ/ፖ/ ወንጀል ምርመራ የተላከ ሪፖርት

  • የሰው ማስረጃ

በ699/2001 መሰረት የዐ/ሕግ ምስክሮች ስም ዝርዝር በክስ ቻርጅ ላይ አልተጠቀሰም

መግለጫተከሳሹ እስር ላይ ነው፡፡

 

 የአቶ እዩእል ሙራቴ ወንጅን የክስ መዝገብ ለማግኘት ይህንን ይጫኑት።

Be the first to comment on "ተከሳሽ: አቶ እዩእል ሙራቴ ወንጅን"

Leave a comment

Your email address will not be published.


*