በቂሊንጦ ቃጠሎ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው 38 እስረኞች የትላንት የፍርድ ቤት ውሎ

kilinto

 

⏩አቃቤ ህግ አራት ምስክሮችን እንዳቀረበ በመግለፅ፤ ጭብጡን አስረዳ ሲባል ተከሳሾቹ በክሳቸው በቀረበው አግባብ መሰረት መሂኑን ተናግሮ ነበረ። በእለቱ ያልተሰየሙትን የችሎቱ መሃል ዳኛ ለሟሟላት የገቡት ዳኛ በሪሁ ዘሪሁን (ፕሬዝዳንት)፤ አቃቤ ህጉ ያቀረበው ጭብጥ ዝርዝር  እና ገላጭ አለመሆኑን ተናግረው በእያንዳንዱ ተከሳሽ ምስክሩ የሚያስረዳውን ነገር (ጭብጥ) በአግባቡ እንዲያስመዘግብ አዘውታል።

⏩ አቃቤ ህጉም (መኩሪያ አለሙ) “እኛ ባናምንበትም ፍርድቤቡ ካዘዘ ..” በማለት ሲጀምር፤ ፕሬዝዳንቱ አቋርጠውት የታዘዘውን ብቻ እንዲያደርግ እና ትእዛዙን በተመለከተም አስተያየት ስጥ አለመባሉን በመግለፅ የታዘዘውን ብቻ እንዲፈፅም እና ሁለተኛ ተመሳሳይ ነገር እንዳይደግም አስጠንቅቀውታል።

⏩ምስክሩ በ2ኛ፣ 38ኛ፣ 33ኛ፣ 32ኛ እና 34ኛ ተከሳሾች ላይ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ነሐሴ 28/2008 ቀን በቃጠሎው ወቅት ተሳታፊ መሆናቸውን እና ከእለቱ አስቀድሞም ዝግጅት እንደነበረ የሚመሰክር መሆኑን አቃቤህግ በጭብጥነት አስመዝግቧል።

በመጀመሪያ የቀረበው ምስክር የሰጠው ምስክርነት

👉አቶ በድሉ በላይ ይባላል። በቂሊንጦ ቃጠሎ ወቅት በዞን 2 የ5ኛ ቤት ከታሳሪዎች መሃል የተመረጠ አስተዳደር መሆኑን ተናግሯል።

👉ምስክሩ የሚመሰክርባቸው ተከሳሾች፤ ወልዴ ሞቱማ፣ ቶፊክ ሽኩር፣ ሸምሱ ሰይድ፣ ከድር ታደለ እና ሲሳይ ባቱ እንደሚባሉ ጠቅሶ፤ ወልዴ ሞቱማን፣ ቶፊክ ሽኩርን እና ሸምሱ ሰይድን ብቻ በችሎት ለይቶ አሳይቷል።

👉ዳኞች የተቀሩትን ሊመሰክርባቸው የመጣባቸውን ተከሳሾችች ለምን መለየት እንዳልቻለ ሲጠይቁት፤ ካሉት ተከሳሾች ውስጥ ስላላያቸው መሆኑን ተናግሮ ነበር። ነገር ግን አቃቤ ህግ በድጋሜ ሲጠይቀው መለየት ስላልቻለ መሆኑ ተናግሯል።

👉ሸምሱ ሰይድ በ28/12/2008 ጠዋት ላይ ዩኒፎርሙን አውጥቶ “ይሄን ያላወለቀ ቡሽቲ ነው እናቱ ትበዳ” ብሎ ሁሉም ተከሳሾች እንዲያወልቁ ማድረጉን

👉 በግሩፕ የመደራጀት ነገር እንደነበር፤ ወልዴ ሞቱማ በሽብር ተከሶ እንደመጣ እና በተለያዩ አካባቢዎች ለሞቱ ሰዎች የህሊና ፀሎት እናደርጋለን እያለ እንደሚሰበስብ፤ በተጨማሪም አልጋ ላይ ይሰባሰቡና የኦነግን አላማ እንደሚደግፉ እና እንደሚቀላቀሉም እንደሚያወሩ

👉ድምፃችን ይሰማ የሚባል ግሩፕ እንዳለ፤ ክሳቸው ምን እንደሆነ እንደማያውቅ ግን ሽብር እንደሚመስለው፤ ከድር ታደለ የቃጠሎው ቀን “ምግብ አንበላም ድምፃችን ይሰማ ቤተሰቦቻችን ይስሙልን” በማለት ጮክ ብሎ ሲናገር እንደነበር

👉 ከድር ታደለ የድምፃችን ይሰማ አባል መሆኑን ሲናገር ሰምቶት ያውቅ እንደሆነ ምስክሩ ተጠይቆ አባል ነኝ ብሎ ሲናገር ሰምቶት እንደማያውቅ ግን ሌላ ነው አባል መሆኑን እንደነገረው

👉ሲሳይ ባቱ የሚባለው ተለሳሽ እሳት ይዞ 5ኛ ቤት የሚገኝ የተደረደረ ፍራሽ ላይ እንደለኮሰው፤

👉 ሲሰይ ፍራሹ ላይ ሲለኩስ የት ሆኖ እንዳየው ሲጠየቅ፤ በአይኑ እንዳላየ ነገር ግን ሸዋሮቢት ምርመራ ሰአት ላይ ከሰጠው ቃል እንደተረዳ

👉 ቶፊክ ሽኩር እና ሸምሱ ሰይድ ነፃነት አበበ የሚባል እስረኛ ሲደበድቡ እንደነበር እና በኋላ ላይም ነፃመት ሞቷል የሚባል ወሬ መስማቱን

👉ወልዴ ሞቱማ በቃጠሎው ቀን ሲሯሯጥ እንደነበር፤ “ፖሊሶች የሉም ወደውጪ እንውጣ” ሲል እንደነበር

👉ተሰብስበው በግሩፕ የሚያወሩት ስለተከሰሱበት ጉዳይ ይሁን አይሁን እንደማያውቅ

👉ብዙ ታራሚዎች ምግብ አንበላም ብለው ሲናገሩ እንደነበረ፤ የከድር ታደለ የሚለየው ጮክ ብሎ “ድምፃችን ይሰማ ቤተሰቦቻችን ይስሙልን” ስላለ መሆኑን

👉 ለቃጠሎው መንስኤ የሆነው የቤተሰብ ምግብ መከልከሉ መሆኑን

👉በወቅቱ የእሳት ጭስ፣ ተኩስ እና የአድማ በታኝ ጭስ እንደነበረ እና እስረኞች ተዘግቶ የነበረውን የውጪ (የዞን) በር ሰብረው መውጣታቸውን

መስክሮ ተመልሷል።

ሁለተኛው ምስክር ሰለሞን አስፋው እንደሚባል እና በ20ኛ ተከሳሽ አጥናፉ አበራ በ28/12/2008 ቀን የነበረውን ተሳትፎ እና ከዛ በፊትም ዝግጅት እንደነበረ የሚያስረዳ ምስክር መሆኑ በአቃቤ ህግ ተገልፇል።

ሁለተኛው ምስክር የሰጠው ምስክርነት

👉ምስክሩ በወቅቱ ከአጥናፉ ጋር ዞን አንድ 6ኛ ቤት አብረው እንደነበሩ ገልፇል። አጥናፉንም ከችሎት ለይቶ አሳይቷል። በአሁኑ ሰአት ከእስር ተፈቶ በቦሌ ክፍለከተማ የሚገኝ ወረዳ ውስጥ ኮሚኒኬሽን ኦፊሰር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ተናገሯል።

👉 አጥናፉ፤ ስለ ግንቦት 7 እንቅስቃሴ በቤት ውስጥ እና ግቢ ውስጥ ላሉ እስረኞች መግለጫ እንደሚሰጥ፤

👉”ከጎንደር ይመጡ የነበሩ እህል የጫኑ መኪኖች ተቃጠሉ፤ ኢህአዴግ እሱ ወያኔ ነው የሚለው ፥ ወያኔ 3 ወር ቀራት እያለ” ታራሚው በኢህአዴግ ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ የማድረግ ስራ ይሰራ እንደነበር እና ወሬዎችን ያሰራጭ እንደነበር

👉 ምስክሩ “በወቅቱ እርስ በኢህአዴግ ተስፋ ቆርጦ እንደነበረ ሲጠየቅ

👉ግንቦት 7 በኢህአዴግ ላይ አብላጫ እንዲኖረው እና ከግቢ ውጪ ያለው ነገር ሰላማዊ እንዳልነበር ያወራ እንደነበር

👉 በቴሌቭዢን መግለጫ ሲሰጥ ጮክ ብሎ የማጥላላት ወሬ እንደሚናገር ፣ ባለስልጣናት ሲታዩ ውሸታም እንደሚል፤ ቻናል እስከማስቀየርም እንደሚደርስ

👉በ26/12/2008 ማታ ላይ የቤተሰብ ምግብ የማይገባ ከሆነ የማረሚያ ቤቱንም አንበላም፤ አተት ያለበት የማረሚያ ቤቱ እንጂ የቤተሰብ ምግብ እንዳለወሆነ ሲናገር እንደሰማው

👉በ28/12/2008 ጠዋት ውጪ ላይ ተኩስ ከቅርበት ይሰማ እንደነበር፣ ይኖሩበት የነበረው ዞን ግቢ ውስጥ እሳትም ይቃጠል እንደነበር፣ አጥናፍ በወቅቱ ከአልጋ ላይ ብረት አንስቶ እያስፈራራ እስረኞች ከቤቱ እንዲወጡ ሲያስገድድ እንደነበረ፤ እሱን (ምስክሩን) ግን እንዳላስገደደው፣ በዛ ሰአት ከቤት መውጣት ማለት በጥይት መመታት ማለት እንደሆነ

👉  አጥናፍ እስረኞችን እንዲወጡ ሲያደርግ “ወንድሞቻችን እየሞቱ እየተገደሉ እኛ ቁጭ አንልም” ሲል እንደነበረ፤

👉አጥናፍ “ወንድሞቻችን እየሞቱ   .. ” ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ምስክሩ ተጠይቆ ነበር። አንድ እስረኛ ከቤት ወጥቶ ግቢ ውስጥ እያለ እግሩን በጥይት ተመቶ ተመልሶ መምጣቱን በማየቱ እንደሆነ

👉 አጥናፍ ውጡ ብሎ ካስወጣቸው መሃል በጥይት የተመታ እስረኛ እንደሌለ

👉 ለቂሊንጦ ቃጠሎ ዋነኛው መንስኤ የምግብ መከልከሉ መሆኑን፤ በሁለተኝነት ግን በግቢ ውስጥ ይናፈሱ የነበሩ ወሬዎች እስረኛውን ተስፋ ያስቆርጡት ስለነበር መሆኑን

መስክሮ ተመልሷል።

⏩አቃቤ ህግ አቅርቧቸው የነበሩት አራት ምስክሮች ነበሩ። ሆኖም ሁለቱ ምስክሮች የሰጡት ምስክርነት በቂው እንደሆነ በመናገሩ ቀሪዎቹ ሳይመሰክሩ እንዲመለሱ ተደርጓል።

⏩ቀሪ ምስክሮችን ለማቅረብ ፖሊስ የተያዘው ቀጠሮ ለትላንት ብቻ እንደተያዘ በማሰብ ምላሽ ማቅረቡን አቃቤህግ የተናገረ ሲሆን ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ያሉ 4ት ምስክሮቹን እንዲቀርቡለት መጥሪያ እንዲወጣለት ጠይቋል።

⏩ ተከሳሾች ለ5ወር የተሰጣቸው ቀጠሮ አቃቤ ህግ ምስክሮቹን ፈላልጎ እንዲያቀርብ በቂ ጊዜ እንዲኖረው ተብሎ መደረጉን ገልፀው፤ ከ5 ወር በኋላ ቆይተው ሲመጡ ፖሊስ ለ2ት ሳምንት የተያዘውን ቀጠሮ አላውቀም ማለቱ አሳማኝ እንዳልሆነ፤ እንዲሁም ከማረሚያ ቤት አቀርባቸዋለው ያላቸውን ምስክሮች አቃቤህግ ያስጠናቸው ምስክሮች እንጂ  በባለፈው ቀጠሮ ከማረሚያ ቤት የሚቀርቡ ምስክሮችን መጨረሱን ገልፆ እንደነበር በብስጭት ተናግረዋል።

⏩በእለቱ ያልተሰየሙትን የመሃል ዳኛ ለሟሟላት የገቡት ዳኛ በሪሁ ዘሪሁን (ፕሬዝዳንት)፤ አቃቤ ህግ ከፖሊስ ጋር በመሆን በቅርበት በመስራት ምስክሮቹን እንዲቀርቡ ማድረግ የሱ ግዴታ መሆኑን በመግለፅ፤ ፖሊስ የተያዘውን ቀጠሮ አላወቀም የሚለው ምላሽ ተቀባይነት እንደማይኖረው በመግለፅ ቀሪ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ለዛሬ ታህሳስ 24/2010 ተቀጥሯል።

  ሙሉ ክሱን ለማየት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።

በእንግሊዘኛ የተተረጎመ የክስ ዝርዝር እንዲሁም የተከሳሾችን ፎቶዎች ለማግኘት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።

Be the first to comment on "በቂሊንጦ ቃጠሎ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው 38 እስረኞች የትላንት የፍርድ ቤት ውሎ"

Leave a comment

Your email address will not be published.


*