በሽብር ወንጀል የተከሱ አራት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

Ato Tilahun

 

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አባል በመሆን የሽብር ተግባር ለመፈጸም  ተንቀሳቅሳችዋል ተብለው የተከሰሱ አራት ግለሰቦች በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት በእስራት ተቀጡ።

ተከሳሾቹም:

1ኛ ጥላሁን ኦዴሳ

2ኛ አደም ሁሴን፣

3ኛ ረጉማ ተሰማ እና

4ኛ ያዴሳ ነጋሳ ናቸው።

በዚህም መሰረት 1ኛ ተከሳሽ 4 አመት ከ9 ወር፣ 2ኛ ተከሳሽ 5 አመት ከ6 ወር፣ 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ደግሞ እያንዳንዳቸው 4 አመት ከ8 ወር እንዲታሰሩ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት ውሳኔ አስተላልፏል።

ከሳሾቹ ፍርድ ቤት ቀርበው  ድርጊቱን አልፈጸምንም በማለት ተከራክረው ነበር ሆኖም ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ብሏቸዋል::

1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ነዋሪነታቸው ኬንያ የነበረ ሲሆን 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሽ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ደርሚ ከተማ ነዋሪዎች ናቸው።

አቃቢ ህግ ተከሳሾቹ የኦነግ ቡድን አባል በመሆን  ወታደራዊና ፖለቲካዊ ስልጠና በመውሰድ፥ ለሽብር ቡድኑ አባላት የተለያዩ ሃገራዊ መረጃዎችን በማቀበል ለሽብር ተግባር ሲንቀሳቀሱ ነበረ ብሎ ነው የወነጀላቸው::

 

እነ ጥላሁን ኦዴሳ በአሁን ሰአት ኢትዮጽያ ውስጥ በ95 የክስ መዝገብ በሽብር ተከሰው ከሚገኙ 916 ኢትዮጽያውያን መካከል ናቸው።

 

Be the first to comment on "በሽብር ወንጀል የተከሱ አራት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ"

Leave a comment

Your email address will not be published.


*