በሽብር ክስ ቀርቦበት ክሱን ቂሊንጦ ሆኖ እየተከታተለ የሚገኝው አስቻለው ደሴ አስቸኳይ ህክምና እንደሚያስፈልገው ቢናገርም ሌላ ቀጠሮ ተሰጠው

Aschalew Dessie

የዜናው ምንጭ ማህሌት ፋንታሁን

አስቻለው ደሴ በሽብር ክስ ቀርቦበት ክሱን ቂሊንጦ ሆኖ እየተከታተለ የሚገኝ ወጣት ነው። ማእከላዊ በምርመራ ወቅት በድብደባ ብልቱ የተኮላሸበት መሆኑን ከዚህ በፊት በፍርድ ቤት ልብሱን አውልቆ አሳይቷል። አስቸኳይ ህክምና እንደሚያስፈልገው እና የዘር ፍሬው ካልወጣ ወደ ካንሰር እንደሚቀየርበት ጳውሎስ ሆስፒታል ባለ ሃኪም ተነግሮት ለጥር 27/2010 እንዲቀርብ ቀጠሮ ተሰጥቶት ነበር። የቂሊንጦ ሃላፊዎች ግን የቀጠሮውን ቀን አሳልፈው የቀጠረው ሃኪም በሌለበት/በማይገኝበት ጥር 29/2010 ቀን ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ወስደውት ለግንቦት 17/2010 ተለወጭ ቀጠሮ እንደተሰጠው ነግረውታል።

ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ የህመሙ ሁኔታ አስቸኳይ እና ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ የቂሊንጦ ሃላፊዎች ሆስፒታል በአስቸኳይ እንዲወስዱት እንዲፈቀድለት ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም ዳኞቹ ሆስፒታል በሰጠው ቀጠሮ ማዘዝ እንደማይችሉ ነግረውታል። ቂሊንጦም የሚገኘው ጨለማ ቤት እንደሆነ አቤቱታ አቅርቦ ነበር። ጉዳዩን የሚከታተለው 4ኛ ችሎት በአቤቱታው ላይ ትእዛዝ ለመስጠት ለመጪው አርብ የካቲት 7/2010 ቀጠሮ ሰጥቶታል።

Be the first to comment on "በሽብር ክስ ቀርቦበት ክሱን ቂሊንጦ ሆኖ እየተከታተለ የሚገኝው አስቻለው ደሴ አስቸኳይ ህክምና እንደሚያስፈልገው ቢናገርም ሌላ ቀጠሮ ተሰጠው"

Leave a comment

Your email address will not be published.


*